We use cookies and other technologies on this website to enhance your user experience.
By clicking any link on this page you are giving your consent to our Privacy Policy and Cookies Policy.
ስንክሳር icon

4.8.1 by Samuel Minale


Mar 21, 2024

About ስንክሳር

English

ስንክሳር ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Sinksar the Orthodox Tewahedo Church in Amharic and English

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

ስንክሳር ማለት የእግዚአብሔርን ረድኤት አጋዥ በማድረግ በበጎ ስጦታውም የተሰበሰበ ማለት ነው።

ይህ ሃይማኖቶታቸው የቀና የከበሩ አባቶች ፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከነቢያት ፣ ከሐዋርያት ፣ ከሊቃነ ጳጳሳት ፣ ከኤጲስቆጶሳት ፣ ከመነኮሳትም ሁሉ ከገዳማውያንም ከገድሎቻቸው ከመላእከት አለቆችም ከድርሳናቸው የሰበሰቡትና ያቀነባበሩት አምላክን የወለደች እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም ከአደረገቻቸው ድንቆች ተአምራቶችም የክብር ባለቤት የሆነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበዓላቶቹን መታሰቢያ በዘመናት ሁሉ ከመስከረም መባቻ እስከ ዓመቱ ፍፃሜ ሁል ጊዜ ምእመናን እንዲያነቡት እንዲሰሙትም ይሆን ዘንድ ተዘጋጀ።

ይህንንም ቅዱስ መጽሐፍ ሰብስበው ያቀነባበሩት በሽህ ሦስት መቶ ንጹሐን በሆኑ ሰማዕታት ዘመን ነው። የእሊህ የተባረኩ አባቶቻችን ጸሎታቸውና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር።

ለዘላለሙ አሜን!!

የቅዱሳንን ታሪክ ለማንበብ ከታሪካቸውም ለመማር እኛም በክርስትና ህይወታችን እንዲሁም በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በዋነኝነት ቅዱሳኑ እንዲራዱን እንዲያማልዱንም በሌላም መልኩ ከነሱ የክርስትና ህይወት በመነሳት እኛስ ምን ማረግ እንችላለን ከቅዱሳኑ ታሪክ ምንን እማራለው የሚለውን እንድናስብ ይረዳናል ብሎ በማሰብ እንዲሁም በብዙ መፅሃፈ ስንክሳርን ማግኘት በማይችሉ ምእመናን ጥያቄ መሰረት ይህን የሞባይል አፕሊኬሽን ለራሶ እንዲሁም ከጉዋደኞቾ ፣ ቤተሰቦቾ ፣ የስራ ባልደረቦቾ ባጠቃላይ ከወዳጅ ዘመዶቾ ጋር በመሆን ይጠቀሙበት ዘንድ ትልቁን የቤተክርስቲያን መፅሃፍ መፅሃፈ ስንክሳርን ጠቅለንም ባይሆን ፈጣሪ በፈቀደ የቻልነውን ሙሉውን ታሪክ ያልቻልነውን ደግሞ ዋና ታሪኩን ጨምቀን አቅርበናል።

እርሶም እኝህን መንፈሳዊ ታሮኮች ሰአት መድበው በቀን ቢያንስ ከ3—10 ደቂቃ ወስደው የእለቱን ስንክሳር እንዲያነቡ እንዲማሩበት ከወዳጆቾ ጋርም ውይይቶችን እኒዲያረጉበት እንመክራለን።

በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ የተካተቱት ብዙሃኑ ቅዱሳን ከ6ቱ እህታማማች ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አብያተ ክርስትያናት ናቸው

እነዚህም አብያተ-ክርስትያናት:-

- የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

- የ ግብፅ / አሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

- የ ሶሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

- የ አርመንያ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

- የ ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

- የ ህንድ - ማንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

ያንብቡ ያነበቡትንም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመሆን ይወያዩበት - አፕሊኬሽኑንም ለሌላቸው ያካፍሉዋቸው

ድጋፍዎ አስተያየትዎ አይለየን

ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ይደምረን

አሜን!!

በዚህ እለት ማን ቅዱስ እንደሚከብር ያውቃሉ? ከነ ታሪካቸው ገብተው ይመልከቱ ከበረከታቸውም ተካፋይ ይሁኑ። ይህንንም ስራ ሰርቶ ለማጠናቀቅ አመታትን የፈጀ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ አብዛኞቹን ፅሁፎቹን በማዘጋጀት የላቀ ሚና ለተገበረው ለዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ምስጋናችን ከልብ ነው።

ዲ/ን ዮርዳኖስም ለብዙ አመታት እድሜውን ሙሉ መንፈስ ቅዱስ ባቀበለው መጠን ጎንደር በሚገኘዉ በዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ የቅዱሳን ታሪክ በመማር ፣ በማንበብ ፣ በመተርጎም ፣ በመፃፍ ፣ በማዘጋጀት እና በማስተማር ጭምር የኖረ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ ነው። ይህንንም እርሱ ያዘጋጃቸውን ፅሁፎች በነፃ ምዕመንን ለማስተማር በፌስ ቡክ ፣ በቴሌ ግራም እንዲሁም ለኛም በነፃ ሰጥቶን እኛም ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማስተማር እና የቅዱሳን በረከትንም ለኛም ላንባቢውም እንድንካፈል በአፕሊኬሽን መልክ አቅርበናል።

ስንክሳር * Sinksar - (Lives of Saints) in Amharic and English language.

ስንክሳር(የቅዱሳን ታሪክ) ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Sinksar(Synaxarium) the Orthodox Tewahedo Church

In the name of the Father, the Son, and the Holy Spirit, One God Amen!

In order to learn from the Synaxarium or history and Lives of the Christian Saints and to get better in your Christianity especially in Orthodox Tewahedo Church life we highly recommend you to read the book, and for those of you who couldn’t access the book here is an App for it which contain the main stories with pictures illustrating the story.

Most of the Saints are from the Oriental Orthodox Church.

This Oriental Orthodox communion is composed of six autocephalous churches:

- the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church,

- the Coptic Orthodox Church of Alexandria,

- the Syriac Orthodox Church of Antioch,

- the Armenian Apostolic Church,

- the Eritrean Orthodox Tewahedo Church, and

- the Malankara Orthodox Syrian Church.

- In Amharic and English languages.

Keep reading, discuss what you have read with other Christians, and Keep sharing the App for all the Christians of the world.

What's New in the Latest Version 4.8.1

Last updated on Mar 21, 2024

- በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት ስንክሳርን በድምፅ ማዘጋጀት ጀምረናል ይህም ጅማሮ አፕሊኬሽኑ ላይ ተካቷል
- የየወሩን ስንክሳር ወደታች የየቁኑን ደግሞ ወደ ጎን ስክሮል እያረጉ በቀላሉ ማየት እንዲችሉ ተደርጓል
- የእንግሊዘኛው ስንክሳር ተካትቷል
- የአፕሊኬሽኑ መጠን ተቀንስዋል
- ፊት ለፊት ላይ በዛሬው ቀን የሚውሉትን ቅዱሳኖች ዝርዝር ማየት እንድትችሉ ተደርጎዋል
- ካለ ኢንተርኔት እንዲሰራ ተደርጓል
- የቅዱሳን ስዕላት ከነታሪኮቻቸው
- ቅዱሳን የሚውሉበት ቀን ከነታሪኩ
- ፅሁፉን ማስተለቅ ማሳነስ ያስችላል
- ታሪኩን ሼር ማድረግ ያስችላል
- የወሩን ብቻ ለማየት ያስችላል
- The English Synaxarium is Added

Translation Loading...

Additional APP Information

Latest Version

Request ስንክሳር Update 4.8.1

Uploaded by

Trung Hiền

Requires Android

Android 4.1+

Available on

Get ስንክሳር on Google Play

Show More

ስንክሳር Screenshots

Comment Loading...
Languages
Languages
Subscribe to APKPure
Be the first to get access to the early release, news, and guides of the best Android games and apps.
No thanks
Sign Up
Subscribed Successfully!
You're now subscribed to APKPure.
Subscribe to APKPure
Be the first to get access to the early release, news, and guides of the best Android games and apps.
No thanks
Sign Up
Success!
You're now subscribed to our newsletter.